0334400051Facebook
እንኳን ወደ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ድረ-ገጽ በደህና መጡ!

ለህዝባችን እንዴት እንደምናገለግል

የዋግ ኽምራ ገንዘብ መምሪያ የህዝብን ሀብት በኃላፊነት፣ በግልጽነትና በፍትሃዊነት ለማስተዳደር የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና የስራ ሂደቶች ይመልከቱ።

የበጀት ዝግጅትና ክትትል የስራ ሂደት

Mekonnen Zegeye
የሂደቱ አስተባባሪ

መኮነን ዘገየ

የበጀት ዝግጅትና ክትትል የስራ ሂደት አስተባባሪ

ሰቆጣ፣ ዋና መምሪያ
የዋግ ኽምራ ገንዘብ መምሪያ

የዞኑን መደበኛና የካፒታል በጀት ማዘጋጀት፣ ፍትሃዊ የሀብት ድልድልን መምራትና አፈፃፀሙን መከታተል፡፡

የበጀት ዝግጅትና ክትትል የስራ ሂደት የህዝብ ሀብት ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የልማት መስኮች (ትምህርት፣ ጤና፣ መንገድና ንጹህ ውሃ) በፍትሃዊነት እንዲመደብ ስትራቴጂያዊ እቅድ ያወጣል፡፡ ዋና ዋና ተግባራት፦ • ዓመታዊ መደበኛና የካፒታል በጀት ማዘጋጀትና ማስተዳደር • የወረዳዎች የበጀት ድጎማ ቀመሮችን ማዘጋጀትና ማከፋፈል • የበጀት አፈፃፀም ሪፖርቶችን በየሩብ ዓመቱ መገምገም • የዜጎች በጀት (Citizen Budget) አዘጋጅቶ ለህዝብ ማሳወቅ
Share: